የፕላንና ልማት ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በጋራ በመሆን በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ውይይት አካሂደዋል፡፡ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶክተር ፍጹም አሰፋ በአገራችን ኢትዮጵያ ወቅታዊና ሀገራዊ የሆኑ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ፣ ፓለቲካዊ እና በተለያዩ ዘርፎች ላይ በየጊዜው የሚደረጉትን ለውጦችና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ሁሉም የመንግስት ሠራተኞች በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እንደሚያስፈልግ እንዲሁም በዕውቀት ላይ ተመስርተው ስራቸውን በአግባቡ እንዲፈፅሙ ለማስቻል የተዘጋጀ የውይይት መድረክ መሆኑን አስታውቀዋል። ክብርት ሚኒስትሯ ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት እና ሰባት ዓመታት በሀገራችን የመንግስት ለውጥ ካስተናገደች በኋላ የሚጨበጡ እና የሚታዩ ድሎች በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚ እና በፖለቲካ ዘርፎች ማምጣት እንደተቻለ አመላክተው ባለፉት ስድስት እና ሰባት ዓመታት ያስመዘገብናቸው መልካም ስራዎች ያሉብንን ትልልቅ የቤት ስራዎች እንዳያዘናጉን መጠንቀቅ አለብን ብለው ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡ በዕለቱ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ ወቅታዊ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የውይይት ሰነድ አቅርበዋል፡፡ በቀረበውም ገለጻ ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታና ቀጣይ አቅጣጫ ላይ የተፈጠረውን ግንዛቤ መነሻ በማድረግ የፕላንና ልማት ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች የሚጠበቅባቸውን እንዲያደርጉ አቅጣጫ በማስቀመጥ የውይይት መድረኩ ተጠናቋል።
Comments
0 commentsNo comments yet. Be the first to share your thoughts.
Leave a comment
Comments appear right away. Improper language and hate speech are not allowed. You can edit your comment within 30 minutes and delete it anytime on this device.